Jump to content

The Adventures of Robin Hood

ከውክፔዲያ
ሮቢን ሁድ

The Adentures of Robin Hood (የሮቢን ሁድ ዠብዱዎች) ከ1955 እስከ 1959 እ.ኤ.አ. ድረስ በእንግሊዝ አገር የተሠራ ድራማ ሲሆን ስለ አፈ ታሪካዊው ዠብደኛ ሮቢን ሁድኢንግላንድ ንጉሥ ቀደማዊ ሪቻርድ በጀርመን አገር በታሠሩበት ጊዜ ወይም 1193 እ.ኤ.አ. የሚያሳይ ፊልም ነው።

በዚሁ ዘመን የሪቻርድ ወንድም ልዑል ጆህን ኢንግላንድን በእንደራሴነት እያስተዳደሩ፣ የኖርማን ሕዝብም የአገሩ አለቆች ሁነው፣ ሮቢን ሁድ እንደአፈ ታሪኩ የኗሪ አንግሎ-ሳክሶን ወንበዴዎች ወይም አርበኞች ቡደን መሪ ሆኗል።

እንዲያውም አፈ ታሪካዊው ሮቢን የተለያዩ ዕውነተኛ ታሪካዊ ወንበዴዎች በአንድላይ ያዋሕዳል። ከ1200ዎቹ እ.ኤ.አ. ጀምሮ «ሮበሆድ» የሚል ወይም መሳይ መጠሪያ ለልዩ ልዩ አመጸኞች እንደ ተሰጠ ከታሪክ መዝገቦች ይታወቃል። ከ1400 እ.ኤ.አበኋላ ደግሞ የሮቢን ሁድ እና የቡድኑ ትውፊታዊ ቅኔዎች በሰፊሊታወቁ ቻሉ። በመጨረሻ መቼቱ በልብ ወለድ ዘንድ ወደ ቀደማዊ ሪቻርድ ዘመን ተዛወረ።

የሳክሶኖች ወይም የኖርማኖች አነጋገር በ 1193 እ.ኤ.አ. ለዘመናዊ ሰሚዎች ምንም አይገባቸውም ነበርና ተዋናዮቹ ሁሉ በ1950ዎቹ እ.ኤ.አ. መደበኛ በኾነው እንግሊዝኛ ያወራሉ። ከዚህም በላይ አንዳንድ የታሪክ ስኅተቶች ይገኙበታል፤ ለምሳሌ «ግኒ» የተባለው ገንዘብ ከ1700ዎቹ ነበር እንጂ በ1193 እ.ኤ.አ. ምንም አልታወቀም ነበር። ቢሆንም ለመዝናኛው የተወደደና በብዙ አገራት የተሠራጨ ፕሮግራም ሆኖ ቆይቷል::